About Us

Detail about our bureau Gambella Peoples' National Regional State Bureau of Finance

የተቋሙ አደረጃጀትና ስልጣንና ተግባራት የጋምቤላ ህዝቦች ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የፋይናንስ ቢሮ ቀደም ሲል የነበረውን የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ አደረጃጀት በተሻሻለው የክልሉ አስፈጻሚ አካላትን ለማደራጀት በወጣው አዋጅ ቁጥር 205/2014 መሰረት የፋይናንስ ቢሮ የሚል ስያሜ ይዞ በአዋጅ የተሰጡትን ተግባርና ኃላፊነት እየተወጣ ይገኛል፡፡ ቢሮው የክልሉን ኢኮኖሚና ማህበራዊ ልማት ለማሳደግና ዘላቂ ልማት ለማረጋገጥ ቁልፍ ድርሻ ካላቸው ዘርፎች መካከል አንዱ ሲሆን በክልሉ የበጀት ክፍፍል ፍትሃዊ እንዲሆን በማድረግ፣ ከተለያዩ ምንጮች ወደ ክልሉ የሚፈሰውን የልማት ሀብት አቅርቦትና የመንግስታት ትብብር ማዕቀፍ እንዲያድግ በማድረግ፣ የመንግስት ፋይናንስ አስተዳደር አሰራር ስርዓቶችን በሁሉም የአስተዳደር እርከኖች እንዲተገበሩ በማድረግ፣ በክልሉ የሀብት አጠቃቀም ውጤታማነት እንዲሻሻል፣ የግዥና ንብረት አስተዳደር ስርዓት በማሻሻልና ዘመናዊ በማድረግ የሀብት ብክነትን በመቀነስ፣ የሲቪል ድርጅቶችንና ማህበራትን የማስፈፀም አቅም፣ የፕሮጀክቶች አፈፃፀም ክትትልና ግምገማ ስርዓት እና የአገልግሎት አሰጣጥ ማሳደግ እንዲሁም ተቋማዊ የማስፈጸም አቅም ግንባታ እና ድጋፋዊ ክትትልና ግምገማ በማድረግ በአዋጅ የተሰጠውን ስልጣንና ኃላፊነት በመወጣት ላይ ይገኛል፡፡

Mission / Vision / Values

Mission

የተቋሙ ተልዕኮ የመረጃን አስፈላጊነት ከምንጊዜም በላይ ተረድቶ አስተማማኝ መረጃዎችን በማደራጀትና በእነዚህ መረጃዎች ላይ ተመስርቶ ጥናትና ምርምር በማካሄድ የፖሊሲ ሃሳቦችን እያመነጨ የክልሉን የልማት ቅደም ተከተል በማውጣት ህብረተሰቡ የተሳተፈባቸውን ዕቅዶች ማዘጋጀትና መከታተል፣ በቁጠባ ላይ የተመሰረተ የሀብት አጠቃቀም እንዲሰፍን የተቋሙን አቅም ግንባታ በማከናወን፣ ዘመናዊ የመንግስት ፋይናንስ አስተዳደርና ቁጥጥር ስርዓትን በመዘርጋት፣ የፊሲካል ፖሊሲ፣ በማስተባበር፣ አሰራሩን የጠበቀ የግዥ ስርዓት በመዘርጋት እና የንብረት ማስወገድ ስራዎችን በማካሄድ፣ ግልጸኝነትና ተጠያቂነት በሰፈነበት አኳን ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ፍትሃዊ የሀብት አስተዳደር ተግባራዊ እንዲሆን በማድረግ፣ ውጤታማ የሲቪል ድርጅቶችንና ማህበራትን የማስፈፀም አቅም እንዲኖር በማድረግ የክልሉን ማህበረ-ኢኮኖሚያዊና ምጣኔ ሀብታዊ ብልጽግናን ማረጋገጥ

Vision

የተቋሙ ራዕይ የክልሉን ሀብት በብቃት በማስተዳደር የዜጎች ቁሳዊ ፍላጎት፣ እኩል ልማት ተሳታፊነት፣ ፍትሃዊ ተጠቃሚነት እና ነጻነትን በማረጋገጥ የክልሉን ሀብት በዋናነት የተማመነ በሁሉም መስክ መሰረታዊ የኢኮኖሚ ለውጥ መጥቶ ማየትና በክልላችን ፐብሊክ ሰርቪሱ ውስጥ በሚሰጠው ቀልጣፋ አገልግሎት ሁሉም የሚረኩበት እና በልዕቀቱና በውጤቱ መሪ ተቋም መሆን።

Values

የተቋሙ እሴቶች  የሕዝብ አገልጋይነት  ፍትሃዊነት  ቆጣቢነት፣  አሳታፊነት  ውጤታማነት  የስራ ትጋትና ቁርጠኝነት  ህጋዊነት  የሙያ ልቀት  የመማርና የለውጥ ተነሳሽነት  ተጋግዞ በቡድን መስራት  የበለጸገ ኢኮኖሚ መገንባት  በመረጃ ማመን

Staff Members